Gå direkte til innholdet
Life Shaped By Wisdom
Spar

Life Shaped By Wisdom

Forfatter:
pocket, 2012
Amhariska

"ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል" (ያዕ 1፥5)

የጥበብ ጉድለት ማሰብ የማይገባንን እንድናስብና መኖር የማይገባንን እንድንኖር ያደርገናል። ኑሮን ያለ ጥበብ ለመኖር መሞከር መኪናን ያለ ነዳጅ ለመንዳት እንደመሞከር ነው። አብዛኛውን ጊዜ በኑሮ ውስጥ የሚጎድለን ገንዘብ፣ ጓደኛ፣ ስራ፣ እውቀት፣ ዕድል ይመስለናል። በእርግጥ እነዚህ ነገሮች ሲጎድሉን ቶሎ እናውቃቸዋለን። ጥበብ ሲጎድለን ግን ቶሎ አንነቃም። ይህ ብቻ ሳይሆን የጎደለን ጥበብ መሆኑን ስለማናውቅ ቶሎ ብለን ሌላ ነገር እንደጎደለን እናስባለን።

ሰው ገንዘብ ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው ገንዘቡ አይበቃውም፤ ጓደኛ ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው የብቸኝነት ስሜት ተጠቂ ይሆናል ወይም የተሰጡትን ሰዎች በአነጋገርና በግንኙነት አያያዝ ጉድለት ያጣቸዋል፤ ስራ ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው በሚያደርገው ነገርና በውሎው ድካም እንጂ እርካታ አይሰማውም፤ ዕድል ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው ችግርና ተራራ እንጂ ደረጃና ተስፋ አይታየውም፤ የሚወደዱ ውጤቶች የማይወደዱ መንገዶች እንዳሏቸው ባለማስተዋል ያለ መንገድ መዳረሻ በመፈለግ ይባክናል። ስለዚህ የጥበብ ጉድለት ያለንን ሁሉ የሌለን ያደርግብናል።

በዚህ መጽሐፍ ልዩ ልዩ የጥበብ ገጽታዎችና አሠራሮች እጅግ ሰፊ በሆነ ሁኔታ ተተንትነዋል። ኑሮአችንን በጥበብ እንድንኖር በዚህ መጽሐፍ ይህ እውነት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ንጽጽር ከብዙ ምሳሌዎች ጋር ቀርቧል። በማንበብ ራስዎን ይጥቀሙ፤ ከዚያም ቤተሰብዎንና ቤተክርስትያንን ይጥቀሙ።

ISBN
9781087879697
Språk
Amhariska
Vekt
268 gram
Utgivelsesdato
10.4.2012
Forlag
Indy Pub
Antall sider
194