Siirry suoraan sisältöön
????? ????
Tallenna

????? ????

pokkari, 2024
amhara

በዚህ መጽሐፍ የምንመለከተው በዋነኛነት የብርሃንን እንቅስቃሴ እና የወጥ አንጻራዊነት ንድፈ ሐሳብን ነው። በመጀመሪያ ምዕራፍ የመብርሄመግነጢሰት ንድፈ ሐሳቦች እና የማክስዌል ቀመሮች ቀርበዋል ፣ የብርሃንን የመርብርሄመግ ነጢሰት ሞገድ መሆንም እናያለን። በሁለተኛው ምዕራፍ የብርሃንን ሥነበሲራዊ ጸባያት (ጽብርቀትን ፣ ስብረትን) ፣ የብርሃንን ባሕርይ እና ዕይታን በአጭሩ ቀርበዋል። ምዕራፍ ሦስት የአንጻራዊነት መርኅ እና የማክስዌል የመብርሄመግነጢስ ሞገድ ቀመሮች በጋሊሊዮን መስተዛምድ ከአንድ ወጥ ዋቢ ሥራዓት ወደሌላ ዋቢ ሥርዓት ሲሸጋገሩ የአንጻራዊነትን መርኅ እንደሚጥሱ እንዲሁም የብርሃን ሙግደትበኒውተናዊ ሥነእንቅስቃሴ የተለመደውን የቶሎታ ድመራ ሕግ እንደሚጥስ ያሳየውን የፊዛውን እና የብርሃን ፍጥነት በገዋ ውስጥ ከዋቢ ሥርዓት አንጻር የማይለዋወጥ መሆኑን ያሳየውን የማይክለስን እና የሞርሌይን የቤተሙከራ ሥራ ይዟል። ምዕራፍ አራት የአንስታይንን የወጥ አንጻራዊነት ሥነመቸት ንድፈ ሐሳብ ይዟል። በሁሉም ምዕራፎች ውስጥ የተወሰነ የከፍተኛ ርከን ሥነስሌት የሚጠይቁ የሒሳብ ሐረጋት እና ቀመሮች አሉ። በዘርፉ ሠፊ ልምድ የሌላቸው አንባቢዎች ጸሓፊው ያሳተመውን የቅምሮች እና ቀስቶ ሥፍሮች ሥነስሌት መጽሐፍ እና የኒውተናዊ ሥነእንቅስቃሴን በማንበብ እና በመረዳት እንዲጀምሩ ይበረታታሉ። ልምድ ያለው አንባቢም ቢሆን ሥያሜዎችን ለመልመድ ከተጠቀሱት መጻሕፍት እንዲጀመር ይመከራል።

ISBN
9788269358346
Kieli
amhara
Paino
218 grammaa
Julkaisupäivä
10.2.2024
Kustantaja
Hezon Academy
Sivumäärä
156